ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 5:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. የዝማሬህን ጩኸት ከእኔ አርቅ፤የበገናህንም ዜማ አልሰማም።

24. ነገር ግን ፍትሕ እንደ ወንዝ፣ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ።

25. “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣መሥዋዕትንና ቊርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?

26. ለራሳችሁ የሠራችሁትን፣የንጉሣችሁን ቤተ ጣዖት፣የጣዖቶቻችሁን ዐምድ፣የአምላካችሁን ኮከብ አንሥታችሁ ተሸከማችሁ።

27. ስለዚህ ከደማስቆ ወዲያ እንድትሰደዱ አደርጋችኋለሁ፤”ይላል ስሙ የሰራዊት አምላክ የሆነ እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 5