ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 4:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ዝናብ ከለከልኋችሁ፤በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብአደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ሌላው ዝናብ አጥቶ ደረቀ።

8. ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

9. “የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

10. “በግብፅ ላይ እንዳደረግሁት፣መቅሠፍትን ላክሁባችሁ፤ከተማረኩት ፈረሶቻችሁ ጋር፣ጐልማሶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤የሰፈራችሁ ግማት አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግሁ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”ይላል እግዚአብሔር።

11. “ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

12. “ስለዚህ እስራኤል ሆይ፤ እንደዚህ አደርግብሃለሁ፤እንደዚህም ስለማደርግብህ፣ እስራኤል ሆይ፤አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።”

13. ተራሮችን የሚሠራ፣ነፋስን የሚፈጥር፣ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 4