ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 4:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፣ድኾችን የምትጨቁኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን”የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፣

2. ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፤“እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበትትሩፋናችሁ እንኳ በዓሣ መንጠቆየሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል።

3. እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

4. “ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣በየሦስቱ ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።

5. እርሾ ያለበትን እንጀራ የምሥጋናመሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤በፈቃዳችሁም በምታቀርቡት ቊርባን ተመኩ፤እናንት እስራኤላውያን በእነርሱም ተኵራሩ፤ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና፤”ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

6. በየከተማው ሆዳችሁን ባዶ አደረግሁት፤በየመንደሩም የምትበሉትንአሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”ይላል እግዚአብሔር።

7. “መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ዝናብ ከለከልኋችሁ፤በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብአደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ሌላው ዝናብ አጥቶ ደረቀ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 4