ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 3:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ለአዛጦን ምሽግ፣ለግብፅም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤“በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”

10. “ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

11. ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ጠላት ምድሪቱን ይወራል፤ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል፤ ድንኳኖቻችሁንይዘርፋል።”

12. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው ጫፍ ላይ፣በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣እስራኤላውያን ይድናሉ።”

13. “ይህን ስሙ፤ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ” ይላል ጌታ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር።

14. “እስራኤልን ስለ ኀጢአቷ በምቀጣበት ቀን፣የቤቴልን መሠዊያዎች አፈርሳለሁ፤የመሠዊያው ቀንዶች ይቈረጣሉ፤ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 3