ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 3:6-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ሰዎች አይደነግጡምን?ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?

7. በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩንለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሳይገልጥ፣ምንም ነገር አያደርግም።

8. አንበሳ አገሣ፤የማይፈራ ማን ነው?ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ትንቢት የማይናገር ማን ነው?

9. ለአዛጦን ምሽግ፣ለግብፅም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤“በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”

10. “ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

11. ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ጠላት ምድሪቱን ይወራል፤ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል፤ ድንኳኖቻችሁንይዘርፋል።”

12. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው ጫፍ ላይ፣በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣እስራኤላውያን ይድናሉ።”

13. “ይህን ስሙ፤ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ” ይላል ጌታ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር።

14. “እስራኤልን ስለ ኀጢአቷ በምቀጣበት ቀን፣የቤቴልን መሠዊያዎች አፈርሳለሁ፤የመሠዊያው ቀንዶች ይቈረጣሉ፤ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

15. የክረምቱን ቤት፣ከበጋው ቤት ጋር እመታለሁ፤በዝሆን ጥርስ ያጌጡ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፤ታላላቅ አዳራሾችም ይፈርሳሉ፤”ይላልእግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 3