ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 3:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ቍሻሻ እደፋብሻለሁ፤እንቅሻለሁ፤ማላገጫም አደርግሻለሁ።

7. የሚያዩሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሹ፣‘ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል?’ ይላሉ፤የሚያጽናናሽንስ ከወዴት አገኛለሁ?”

8. አንቺ በዐባይ ወንዝ አጠገብ ካለችው፣በውሃ ከተከበበችው፣ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን?ወንዙ መከላከያዋ፣ውሃውም ቅጥሯ ነው።

9. ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 3