ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 3:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ፤ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልበዋለሁ፤ዕርቃንሽን ለአሕዛብ፣ኀፍረትሽንም ለነገሥታት አሳያለሁ።

6. ቍሻሻ እደፋብሻለሁ፤እንቅሻለሁ፤ማላገጫም አደርግሻለሁ።

7. የሚያዩሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሹ፣‘ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል?’ ይላሉ፤የሚያጽናናሽንስ ከወዴት አገኛለሁ?”

8. አንቺ በዐባይ ወንዝ አጠገብ ካለችው፣በውሃ ከተከበበችው፣ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን?ወንዙ መከላከያዋ፣ውሃውም ቅጥሯ ነው።

9. ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።

10. ይሁን እንጂ በምርኮ ተወሰደች፤ተሰዳም ሄደች።በየመንገዱ ማእዘን ላይ፣ሕፃናቷ ተፈጠፈጡ፤በመሳፍንቷ ላይ ዕጣ ተጣለ፤ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 3