ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 3:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ምሽጎችሽ ሁሉ ሊበሉ እንደ ደረሱየመጀመሪያ በለስ ፍሬ ናቸው፤በሚወዛወዙበት ጊዜ፣ፍሬዎቹ በበላተኛው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።

13. እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ሁሉም ሴቶች ናቸው!የምድርሽ በሮች፣ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቶአቸዋል።

14. ለከበባው ውሃ ቅጂ፤መከላከያሽን አጠናክሪ፤የሸክላውን ዐፈር ፈልጊ፤ጭቃውን ርገጪ፤ጡቡንም ሥሪ።

15. በዚያ እሳት ይበላሻል፤ሰይፍ ይቈርጥሻል፤እንደ ኵብኵባም ይግጥሻል።እንደ ኵብኵባ እርቢ፤እንደ አንበጣም ተባዢ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 3