ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 3:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለደም ከተማ ወዮላት!ሐሰት፣ዘረፋም ሞልቶባታል፤ብዝበዛዋ ተግዞ አያልቅም።

2. የጅራፍ ድምፅ፣የመንኰራኵር ኳኳቴ፣የፈጣን ፈረስ ኮቴ፣የሠረገሎች ድምፅ ተሰምቶአል

3. ፈረሰኛው ይጋልባል፤ሰይፍ ይንቦገቦጋል፤ጦር ያብረቀርቃል፤የሞተው ብዙ ነው፤ሬሳ በሬሳ ሆኖአል፤ስፍር ቍጥር የለውም፤መተላለፊያ አልተገኘም።

4. ይህ ሁሉ የሆነው ቅጥ ባጣች፣አሳሳችና መተተኛ በሆነች ዘማዊት ምክንያት ነው፤እርሷም በዝሙቷ አሕዛብን፣በጥንቈላዋም ሕዝቦችን ባሪያ ያደረገች ናት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 3