ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 2:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል።

4. ሠረገሎች በአደባባይ ወዲያ ወዲህ ይከንፋሉ፤በመንገዶችም ላይ ይርመሰመሳሉ፤የሚንበለበል ፋና ይመስላሉ፤እንደ መብረቅም ይወረወራሉ።

5. ምርጥ ተዋጊዎቹን ይጠራል፤ዳሩ ግን መንገድ ላይ ይሰናከላሉ፤ወደ ከተማዪቱ ቅጥር ይሮጣሉ፤መከላከያ ጋሻውም በቦታው አለ።

6. የወንዙ በር ወለል ብሎ ተከፈተ፤ቤተ መንግሥቱም ወደቀ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 2