ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 1:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ነነዌ ጥፋት የተነገረ ንግር፤ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፤

2. እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር የሚበቀል፣ በመዓትም የተሞላ ነው። እግዚአብሔር ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤በጠላቶቹም ላይ ቍጣውን ያመጣል

3. እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ በኀይሉም ታላቅ ነው፤ እግዚአብሔር በደለኛውን ሳይቀጣ አያልፍም፤መንገዱ በዐውሎ ነፋስና በማዕበል ውስጥ ነው፤ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 1