ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ነህምያ 7:67-73 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

67. ይህ 7,337 የወንድና የሴት አገልጋዮቻቸውን አይጨምርም፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው።

68. 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣

69. 435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው።

70. አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዡም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።

71. ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 የብር ምናን ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።

72. የቀረው ሕዝብ ባጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 የብር ምናንና 67 አልባሰ ተክህኖ ነበር።

73. ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ነህምያ 7