ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ነህምያ 7:64-72 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

64. እነዚህ የየቤተ ሰብ ትውልድ ሐረጋቸውን ከመዝገብ ለማግኘት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ።

65. ስለዚህም አገረ ገዡ በኡሪምና በቱሚም አገልግሎት የሚሰጥ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።

66. የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤

67. ይህ 7,337 የወንድና የሴት አገልጋዮቻቸውን አይጨምርም፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው።

68. 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣

69. 435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው።

70. አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዡም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።

71. ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 የብር ምናን ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።

72. የቀረው ሕዝብ ባጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 የብር ምናንና 67 አልባሰ ተክህኖ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ነህምያ 7