ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ነህምያ 11:15-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ከሌዋውያኑ፦የቡኒ ልጅ፣ የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሻማያ፤

16. እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት የውጩ ሥራ ኀላፊዎች የነበሩት፣ ከሌዋውያን አለቆች ሁለቱ ሳባታይና ዮዛባት።

17. በምስጋናና በጸሎት ጊዜ ይመራ የነበረው የዋናው አለቃ የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ፣ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የሆነው በቅበቃር፣ የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙስ ልጅ አብድያ።

18. በቅድስቲቱ ከተማ ውስጥ የነበሩት የሌዋውያኑ ቍጥር 284 ነበረ።

19. በር ጠባቂዎች፦ዓቁብ፣ ጤልሞንና በሮቹን የሚጠብቁ ወንድሞቻቸው፣ 172 ሰዎች።

20. የቀሩት እስራኤላውያንም ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋር በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በየርስታቸው ተቀመጡ።

21. የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች በዖፌል ኰረብታ ላይ ተቀመጡ፤ ሲሐና ጊሽጳ በእነርሱ ላይ ያዙ ነበር።

22. በኢየሩሳሌም የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሻብያ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበረ፤ ኦዚ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ለሚዘመረው መዝሙር ኀላፊ ከነበሩት ከአሳፍ ዘሮች አንዱ ነበረ።

23. መዘምራኑ የየዕለቱን ተግባራቸውን በሚቈጣጠረው በንጉሡ ትእዛዝ ሥር ነበሩ።

24. የይሁዳ ልጅ የዛራ ዘር የሆነው የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ሕዝቡን በሚመለከት ጒዳይ ሁሉ የንጉሡ ተወካይ ነበር።

25. ከይሁዳ ሕዝብ ጥቂቱ በመንደሮችና በእርሻ ቦታዎች፣ በቂርያት አርባቅና በዙሪያዋ ባሉ መኖሪያዎቿ፣ በዲቦንና በመኖሪያዎቿ፣ በይቀብጽኤልና በመንደሮቿ ተቀመጡ፤

26. በኢያሱ፣ በሞላዳ፣ በቤትጳሌጥ፣

27. በሐጸርሹዓል፣ በቤርሳቤህና በመኖሪያዎቿ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ነህምያ 11