ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ነህምያ 11:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መሪዎች መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከቀረው ሕዝብ ከዐሥር አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፣ የቀሩት ዘጠኙ እጅ ደግሞ በየራሳቸው ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ ተጣጣሉ።

2. ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በራሳቸው ፈቃድ የተነሣሡትን ሰዎች ሁሉ አመሰገኑ።

3. እንግዲህ በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃዪቱ መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ በዚህ ጊዜም በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የተወሰኑ እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች እያንዳንዳቸው በተለያዩ ከተሞች ባለ በየራሳቸው ንብረት ላይ ተቀመጡ፤

4. ከይሁዳና ከብንያም ወገን የሆኑት የተቀሩት ሰዎች ደግሞ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ከይሁዳ ዘሮች፦ከፋሬስ ዘር የመላልኤል ልጅ፣ የሰፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የዖዝያ ልጅ አታያ፤

5. ከሴሎ ዘር የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ የፆዛያ ልጅ፣ የኮልሖዜ ልጅ፣ የባሮክ ልጅ መዕሤያ።

6. በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ዘሮች በጠቅላላ 468 ብርቱ ሰዎች ናቸው።

7. ከብንያም ዘሮች፦የየሻያ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ፣ የመዕሤያ ልጅ፣ የቆላያ ልጅ፣ የፈዳያ ልጅ፣ የዮእድ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤

8. ተከታዮቹም ጌቤና ሳላይ 928 ወንዶች፤

9. የእነዚህም አለቃ የዝክሪ ልጅ ኢዩኤል ሲሆን፣ የሐስኑአ ልጅ ይሁዳ የከተማዪቱ “ሁለተኛ አውራጃ” የበላይ ነበር።

10. ከካህናቱ፦የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፤ ያኪን፤

11. የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ፤

12. የቤተ መቅደሱን ሥራ ያከናወኑት ወንድሞቻቸው፣ 822 ሰዎች፤ የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የአማሲ ልጅ፣ የፈላልያ ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤

13. ወንድሞቹ የሆኑት የየቤተ ሰቡ አለቆች 242 ወንዶች፤ የኢሜር ልጅ የምሺሌሞት ልጅ፣ የአሕዛይ ልጅ፣ የኤዝርኤል ልጅ አማስያ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ነህምያ 11