ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 3:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. “በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩ፣ተስማምተው እንዲያገለግሉት፣አንደበታቸውን አጠራለሁ።

10. ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ፣የሚያመልኩኝ፣ የተበተኑት ሕዝቤቊርባን ያመጡልኛል።

11. በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ፣በዚያ ቀን አታፍሩም፤በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን፣ከዚህች ከተማ አስወግዳለሁና፤ከእንግዲህ ወዲያ፣በቅዱስ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም።

12. በእግዚአብሔር ስም የሚታመኑትን፣የዋሃንንና ትሑታንን፣በመካከላችሁ አስቀራለሁ።

13. የእስራኤል ትሩፋን ኀጢአት አይሠሩም፤ሐሰትም አይናገሩም፤በአንደበታቸውም ተንኰል አይገኝም።ይበላሉ፤ ይተኛሉ፤የሚያስፈራቸውም የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 3