ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 3:14-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ዘምሪ፤እስራኤል ሆይ፤ እልል በይ፤የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ።

15. እግዚአብሔር ቅጣትሽን አስወግዶታል፤ጠላቶችሽን ከአንቺ መልሶአል፤የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ከእንግዲህ ወዲያ አንዳች ክፉ ነገር አትፈሪም።

16. በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን እንዲህይሏታል፤“ጽዮን ሆይ፤ አትፍሪ፤እጆችሽም አይዛሉ።

17. እግዚአብሔር አምላክሽ በመካከልሽ አለ፤እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤በፍቅሩ ያሳርፍሻል፤በዝማሬም በአንቺ ላይ ከብሮ ደስ ይሰኛል።”

18. “ስለ ክብረ በዓላት መተጓጐል የተከዝሽበትን፣የስድብሽን ሸክም፤ከአንቺ አስወግዳለሁ።

19. በዚያ ጊዜ፣ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤አንካሶችን እታደጋለሁ፤የተበተኑትንም እሰበስባለሁ፤በተዋረዱበት ምድር ሁሉ፣ለውዳሴና ለክብር አደርጋቸዋለሁ።

20. በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ፤ያን ጊዜ ወደ አገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ዐይናችሁ እያየ፣ምርኮአችሁን በምመልስበት ጊዜ፣መከበርንና መወደስን፣በምድር ሕዝብ ሁሉ መካከል እሰጣችኋለሁ”፤ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 3