ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 3:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለዐመፀኛዪቱና ለረከሰች፣ለጨቋኞች ከተማ ወዮላት!

2. እርሷ ለማንም አትታዘዝም፤የማንንም ዕርምት አትቀበልም፤ በእግዚአብሔር አትታመንም፤ወደ አምላኳም አትቀርብም።

3. ሹሞቿ የሚያገሡ አንበሶች፣ገዦቿ ለነገ የማይሉ፣የምሽት ተኵላዎች ናቸው።

4. ነቢያቷ ትዕቢተኞች፣አታላዮችም ናቸው፤ካህናቷ መቅደሱን ያረክሳሉ፣በሕግም ላይ ያምፃሉ።

5. በእርሷ ውስጥ ያለው እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ፈጽሞ አይሳሳትም፤በየማለዳው ቅን ፍርድ ይሰጣል፤በየቀኑም አይደክምም፤ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 3