ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 1:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።

7. በልዑል እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤የጠራቸውንም ቀድሶአል።

8. በእግዚአብሔር የመሥዋዕት ቀን፣መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 1