ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 1:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣በረጃጅም ግንቦች ላይ፣የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።

17. እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና።ደማቸው እንደ ትቢያ፣ሥጋቸውም እንደ ጒድፍ ይጣላል።

18. በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው፣ሊያድናቸው አይችልም፤መላዪቱ ምድር፣በቅናቱ ትበላለች፤በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 1