ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 1:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ሀብታቸው ይዘረፋል፤ቤታቸው ይፈራርሳል፤ቤቶች ይሠራሉ፤ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ወይን ይተክላሉ፤ጠጁን ግን አይጠጡም።

14. “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤ በእግዚአብሔር ቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤

15. ያ ቀን የመዓት ቀን፣የመከራና የጭንቀት ቀን፣የሁከትና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤

16. ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣በረጃጅም ግንቦች ላይ፣የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።

17. እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና።ደማቸው እንደ ትቢያ፣ሥጋቸውም እንደ ጒድፍ ይጣላል።

18. በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው፣ሊያድናቸው አይችልም፤መላዪቱ ምድር፣በቅናቱ ትበላለች፤በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 1