ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 1:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2. “ማንኛውንም ነገር፣ከምድር ገጽ አጠፋለሁ”ይላል እግዚአብሔር።

3. “ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤የሰማይን ወፎች፣የባሕርንም ዓሦች አጠፋለሁ፤ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ፣ክፉዎች የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ”ይላል እግዚአብሔር።

4. “እጄን በይሁዳ፣በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤የበኣልን ትሩፍ፣የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤

5. የሰማይን ሰራዊት ለማምለክ፣በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን፣ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፣ በስሙም እየማሉ፣በሚልኮምም ደግሞ የሚምሉትን፣

6. እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።

7. በልዑል እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤የጠራቸውንም ቀድሶአል።

8. በእግዚአብሔር የመሥዋዕት ቀን፣መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።

9. በዚያን ቀን፣በመድረኩ ላይ የሚዘሉትን ሁሉ፣የአማልክቶቻቸውን ቤት፣በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 1