ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 4:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. መሳፍንቶቻቸው ከበረዶ ይልቅ ብሩህ፣ከወተትም ይልቅ ነጭ ነበሩ፤ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቍ የቀላ፣መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበር።

8. አሁን ግን ከጥላሸት ይልቅ ጠቍረዋል፤በመንገድም የሚያውቃቸው የለም፤ቆዳቸው ከዐጥንታቸው ጋር ተጣብቆአል፤እንደ ዕንጨትም ደርቀዋል።

9. በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣በራብ ደርቀው ያልቃሉ።

10. ሕዝቤ ባለቀበት ጊዜ፣ምግብ እንዲሆኑአቸው፣ርኅሩኆቹ ሴቶች በገዛ እጆቻቸው፣ልጆቻቸውን ቀቀሉ።

11. እግዚአብሔር ለመቅሠፍቱ መውጫ በር ከፈተ፤ጽኑ ቍጣውን አፈሰሰ፤መሠረትዋን እንዲበላ፣በጽዮን እሳት ለኰሰ።

12. ጠላቶችም ሆኑ ወራሪዎች፣የኢየሩሳሌምን በሮች ጥሰው ይገባሉ ብለው፣የምድር ነገሥታት፣ወይም ከዓለም ሕዝብ አንዳቸውም አላመኑም።

13. ይህ ግን ከነቢያት ኀጢአት፣ከካህናቷም መተላለፍ የተነሣ ሆኖአል፤በውስጧ፣የጻድቃንን ደም አፍስሰዋልና።

14. እንደ ታወሩ ሰዎች፣በየመንገዱ ላይ ይደናበራሉ፤ማንም ሰው ደፍሮ ልብሳቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ፣በደም እጅግ ረክሰዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 4