ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 4:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ወርቁ እንዴት ደበሰ!ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ!የከበሩ ድንጋዮች፣በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።

2. እንደ ወርቅ ይቈጠሩ የነበሩ፣የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች፣የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ!

3. ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት፣ጡታቸውን ይሰጣሉ፤ሕዝቤ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች፣ጨካኞች ሆኑ።

4. ከውሃ ጥም የተነሣ፣የሕፃናት ምላስ ከላንቃቸው ጋር ተጣበቀ፤ልጆቹ ምግብ ለመኑ፤ነገር ግን ማንም አልሰጣቸውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 4