ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 9:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አቆመች፤

2. ፍሪዳዋን አረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤ማእዷንም አዘጋጀች።

3. ሴት አገልጋዮቿንም ላከች፤ከከተማዪቱም ከፍተኛ ቦታ ተጣራች።

4. እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣“ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ” አለች።

5. “ኑ፤ ምግቤን ተመገቡ፤የጠመቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።

6. የሞኝነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።

7. “ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።

8. ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድሃል።

9. ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል።

10. “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፤

11. ዘመንህ በእኔ ምክንያት ይረዝማልና፤ዕድሜም በሕይወትህ ላይ ይጨመርልሃል።

12. ጠቢብ ብትሆን ጥበበኛነትህ ለራስህ ነው፤ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ያው አንተው ነህ።”

13. ጥበብ የለሽ ሴት ለፍላፊ ናት፤እርሷም ስድና ዕውቀት የለሽ ናት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 9