ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 8:26-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ምድርን ወይም ሜዳዎቿን፣ወይም ምንም ዐይነት የዓለም ትቢያን ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ።

27. ሰማያትን በዘረጋ ጊዜ፣በውቅያኖስ ላይ የአድማስ ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፤

28. ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፣የውቅያኖስን ምንጮች በመሠረተ ጊዜ፣

29. ለባሕር ድንበርን በከለለ ጊዜ፣ውሆችም የእርሱን ትእዛዝ እንዳያልፉ፣የምድርንም መሠረቶች ወሰን ባበጀ ጊዜ፣

30. በዚያን ጊዜ ከጐኑ ዋና ባለ ሙያ ነበርሁ።ሁል ጊዜ በፊቱ ሐሤት እያደረግሁ፣ዕለት ተዕለት በደስታ እሞላ ነበር፤

31. የእርሱ በሆነው መላው ዓለም ሐሤት እያደረግሁ፣በሰው ልጆች ደስ እሰኝ ነበር።

32. “እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤መንገዴን የሚጠብቁ ቡሩካን ናቸው።

33. ምክሬን አድምጡ፤ ጥበበኞች ሁኑ፤ቸልም አትበሉት።

34. በየለቱ ደጃፌ ላይ የሚጠብቅ፣በበራፌ ላይ የሚጠባበቅ፣የሚያዳምጠኝ ሰው ቡሩክ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 8