ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 8:17-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፤ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።

18. ሀብትና ክብር፣ዘላቂ ብልጽግናና ስኬት በእኔ ዘንድ አሉ።

19. ፍሬዬ ከንጹሕ ወርቅ ይበልጣል፤ስጦታዬም ከነጠረ ብር።

20. እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፤በፍትሕም ጐዳና እጓዛለሁ፤

21. ለሚወዱኝ ብልጽግና እሰጣለሁ፤ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ።

22. እግዚአብሔር ከቀድሞ ሥራዎቹ በፊት፣የተግባሮቹ መጀመሪያ አድርጎ አመጣኝ፡

23. ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ፣ከጥንት ከዘላለም ተሾምሁ።

24. ከውቅያኖሶች በፊት፣የውሃ ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድሁ፤

25. ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ከኰረብቶችም በፊት ተወለድሁ፤

26. ምድርን ወይም ሜዳዎቿን፣ወይም ምንም ዐይነት የዓለም ትቢያን ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 8