ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 6:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልጄ ሆይ፤ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፣ስለ ሌላውም ሰው እጅ መትተህ ቃል ብትገባ፣

2. በተናገርኸው ነገር ብትጠመድ፣ከአፍህ በወጣውም ቃል ብትያዝ፣

3. ልጄ ሆይ፤ ራስህን ለማዳን ይህን አድርግ፤በጎረቤትህ እጅ ስለ ወደቅህ፣ሄደህ ራስህን አዋርድ፤ጎረቤትህን አጥብቀህ ነዝንዘው።

4. ዐይኖችህ እንቅልፍ አይያዛቸው፣ሽፋሽፍቶችህም አያንጐላጁ።

5. ከአዳኝ እጅ እንዳመለጠች ሚዳቋ፣ከአጥማጅ ወጥመድ እንዳፈተለከች ወፍ ራስህን አድን።

6. አንተ ታካች፤ ወደ ጒንዳን ሂድ፤ዘዴውን አስተውለህ ጠቢብ ሁን፤

7. አዛዥ የለውም፤አለቃም ሆነ ገዥ የለውም፤

8. ሆኖም ግን በበጋ ምግቡን ያከማቻል፤በመከርም ወቅት ቀለቡን ይሰበስባል።

9. አንተ ታካች፤ እስከ መቼ ትተኛለህ?ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?

10. ጥቂት ማንቀላፋት፤ ጥቂት ማንጐላቸት፤እጅን አጣጥፎ “እስቲ ጥቂት ልረፍ” ማለት፤

11. ድኽነት እንደ ወንበዴ፣ዕጦትም መሣሪያ እንደ ታጠቀ ሰው ከተፍ ይልብሃል።

12. ወሮበላና ጨካኝ፣ነውረኛ አንደበቱን ይዞ የሚዞር፣

13. በዐይኑ የሚጠቅስ፣በእግሩ ምልክት የሚሰጥ፣በጣቶቹ የሚጠቊም፣

14. በልቡ ተንኰል ክፋትን የሚያውጠነጥን፣ምንጊዜም ጠብ ይጭራል።

15. ስለዚህ በቅጽበት መዓት ይወርድበታል፤በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 6