ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 5:10-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ባዕዳን በሀብትህ እንዳይፈነጥዙ፣ልፋትህም የሌላውን ሰው ቤት እንዳያበለጽግ ነው።

11. በዕድሜህ መጨረሻ ታቃሥታለህ፤ሥጋህና ሰውነትህ ሲከዳህ።

12. እንዲህም ትላለህ፤ “ምነው! ተግሣጽን ጠላሁ፤ልቤስ ምነው! መታረምን ናቀ፤

13. የመምህሮቼን ቃል አልሰማሁም፤አሰልጣኞቼንም አላደመጥኋቸውም፤

14. በመላው ጉባኤ ፊት፣ወደ ፍጹም ጥፋት ተቃርቤአለሁ።”

15. ከገዛ ማጠራቀሚያህ ውሃ፣ከገዛ ጒድጓድህም የሚፈልቀውን ውሃ ጠጣ።

16. ምንጮችህ ተርፈው ወደ ሜዳ፣ወንዞችህስ ወደ አደባባይ ሊፈሱ ይገባልን?

17. ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ባዕዳን አይጋሩህ።

18. ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፤በልጅነት ሚስትህም ደስ ይበልህ።

19. እርሷ እንደ ተወደደች ዋላ፣ እንደ ተዋበች ሚዳቋ ናት፤ጡቶቿ ዘወትር ያርኩህ፤ፍቅሯም ሁል ጊዜ ይማርክህ።

20. ልጄ ሆይ፤ በአመንዝራ ሴት ፍቅር ለምን ትሰክራለህ?የሌላዪቱንስ ሴት ብብት ስለ ምን ታቅፋለህ?

21. የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ ነውና፤እርሱ መሄጃውን ሁሉ ይመረምራል።

22. ክፉውን ሰው የገዛ መጥፎ ሥራው ያጠምደዋል፤የኀጢአቱም ገመድ ጠፍሮ ይይዘዋል።

23. ከተግሣጽ ጒድለት የተነሣ ይሞታል፤ከተላላነቱም ብዛት መንገድ ይስታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 5