ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 31:2-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “ልጄ ሆይ፤ የማሕፀኔ ልጅ ሆይ፤የስእለቴ ልጅ ሆይ፤

3. ጒልበትህን በሴት አትጨርስ፤ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል።

4. “ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤

5. አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፋሉ።

6. ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤

7. ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።

8. “ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።

9. ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 31