ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 31:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ንጉሥ ልሙኤልን እናቱ ያስተማረችው ቃል ይህ ነው፤

2. “ልጄ ሆይ፤ የማሕፀኔ ልጅ ሆይ፤የስእለቴ ልጅ ሆይ፤

3. ጒልበትህን በሴት አትጨርስ፤ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል።

4. “ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤

5. አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፋሉ።

6. ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤

7. ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።

8. “ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።

9. ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”

10. ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል?ከቀይ ዕንቊ እጅግ ትበልጣለች።

11. ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤የሚጐድልበትም ነገር የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 31