ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 3:15-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።

16. በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።

17. መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።

18. ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤የሚይዟትም ይባረካሉ።

19. እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤

20. በዕውቀቱ ቀላያት ተከፈሉ፤ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ።

21. ልጄ ሆይ፤ ትክክለኛ ፍርድንና አስተውሎ መለየትን ጠብቅ፤እነዚህ ከእይታህ አይራቁ፤

22. ለነፍስህ ሕይወት፣ለዐንገትህም ጌጥ ይሆናሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 3