ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 3:12-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ ሁሉ፣ እግዚአብሔርም የሚወደውን ይገሥጻልና።

13. ጥበብን የሚያገኛት፣ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው ቡሩክ ነው፤

14. እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና።

15. ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።

16. በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።

17. መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።

18. ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤የሚይዟትም ይባረካሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 3