ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 3:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ልጄ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤በዘለፋውም አትመረር፤

12. አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ ሁሉ፣ እግዚአብሔርም የሚወደውን ይገሥጻልና።

13. ጥበብን የሚያገኛት፣ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው ቡሩክ ነው፤

14. እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና።

15. ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 3