ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 3:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልጄ ሆይ፤ ትምህርቴን አትርሳ፤ትእዛዛቴን በልብህ ጠብቅ፤

2. ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል።

3. ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው።

4. በዚያን ጊዜ ሞገስንና መልካም ስምን፣በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ ታገኛለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 3