ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 26:6-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በተላላ እጅ መልእክትን መላክ፣የገዛ እግርን እንደ መቊረጥ ወይም ዐመፃን እንደ መጋት ነው።

7. በቂል አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ሰላላ የሽባ ሰው እግር ነው።

8. ለተላላ ክብር መስጠት፣በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።

9. በአላዋቂ አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።

10. ቂልን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው።

11. ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ሁሉ፣ተላላም ቂልነቱን ይደጋግማል።

12. ራሱን እንደ ጠቢብ የሚቈጥረውን ሰው አይተሃልን?ከእርሱ ይልቅ ለተላላ ተስፋ አለው።

13. ሰነፍ፣ “በመንገድ ላይ አንበሳ አለ፤አስፈሪ አንበሳ በአውራ ጐዳና ላይ ይጐማለላል” ይላል።

14. መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ሰነፍም በዐልጋው ላይ ይገላበጣል።

15. ሰነፍ እጁን ወጭት ውስጥ ያጠልቃል፤ወደ አፉ ለመመለስ ግን እጅግ ይታክታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 26