ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 26:22-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል።

23. ክፋትን በልብ ቋጥሮ ለስላሳ ቃል የሚናገር ከንፈር፣በብር ፈሳሽ እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።

24. ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል።

25. ንግግሩ ማራኪ ቢሆንም አትመነው፤ሰባት ርኵሰት ልቡን ሞልቶታልና።

26. ተንኰሉ በሽንገላው ይሸፈን ይሆናል፤ነገር ግን ክፋቱ በጉባኤ ይገለጣል።

27. ጒድጓድ የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ድንጋይ የሚያንከባልልም ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 26