ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 26:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. “ቀልዴን እኮ ነው” እያለባልንጀራውን የሚያታልል ሰውም እንደዚሁ ነው።

20. ዕንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤አሾክሻኪ ከሌለም ጠብ ይበርዳል።

21. ከሰል ፍምን፣ ዕንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣አዋኪ ሰውም ጠብን ያባብሳል።

22. የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል።

23. ክፋትን በልብ ቋጥሮ ለስላሳ ቃል የሚናገር ከንፈር፣በብር ፈሳሽ እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።

24. ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 26