ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 26:16-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይልቅ፣ሰነፍ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥራል።

17. በሌሎች ጠብ ጥልቅ የሚል መንገደኛ፣የውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው።

18. ትንታግ ወይም የሚገድል ፍላጻ እንደሚወረውር ዕብድ፣

19. “ቀልዴን እኮ ነው” እያለባልንጀራውን የሚያታልል ሰውም እንደዚሁ ነው።

20. ዕንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤አሾክሻኪ ከሌለም ጠብ ይበርዳል።

21. ከሰል ፍምን፣ ዕንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣አዋኪ ሰውም ጠብን ያባብሳል።

22. የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል።

23. ክፋትን በልብ ቋጥሮ ለስላሳ ቃል የሚናገር ከንፈር፣በብር ፈሳሽ እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።

24. ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል።

25. ንግግሩ ማራኪ ቢሆንም አትመነው፤ሰባት ርኵሰት ልቡን ሞልቶታልና።

26. ተንኰሉ በሽንገላው ይሸፈን ይሆናል፤ነገር ግን ክፋቱ በጉባኤ ይገለጣል።

27. ጒድጓድ የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ድንጋይ የሚያንከባልልም ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 26