ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 26:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በረዶ በበጋ፣ ዝናብ በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ፣ክብርም ለተላላ አይገባውም።

2. ክንፎቿን እንደምታርገበግብ ድንቢጥ ወይም ቱር እንደምትል ጨረባ፣ከንቱ ርግማንም በማንም ላይ አይደርስም።

3. ለፈረስ አለንጋ፣ ለአህያ መሸበቢያ፣ለተላላ ጀርባም በትር ይገባዋል።

4. ቂልን እንደ ቂልነቱ አትመልስለት፤አለዚያ አንተም ራስህ እንደ እርሱ ትሆናለህ።

5. ቂልን እንደ ቂልነቱ መልስለት፤አለዚያ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።

6. በተላላ እጅ መልእክትን መላክ፣የገዛ እግርን እንደ መቊረጥ ወይም ዐመፃን እንደ መጋት ነው።

7. በቂል አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ሰላላ የሽባ ሰው እግር ነው።

8. ለተላላ ክብር መስጠት፣በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።

9. በአላዋቂ አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።

10. ቂልን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 26