ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 24:22-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ሁለቱም የሚያመጡት መዓት፤ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል?

23. እነዚህም ደግሞ የጠቢባን ምሳሌዎች ናቸው፦በዳኝነት አድልዎ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤

24. በደለኛውን፣ “አንተ ንጹሕ ነህ” የሚለውን፣ሕዝቦች ይረግሙታል፤ መንግሥታትም ያወግዙታል።

25. በደለኛውን፣ “አንተ ጥፋተኛ ነህ” የሚሉት ግን መልካም ነገር ይገጥማቸዋል፤የተትረፈረፈ በረከትም ይወርድላቸዋል።

26. እውነተኛ መልስ መስጠት፣ከንፈርን እንደ መሳም ነው።

27. በደጅ ያለውን ሥራህን ፈጽም፤ዕርሻህን አዘጋጅ፤ከዚያም በኋላ ቤትህን ሥራ።

28. በባልንጀራህ ላይ ያለ ምክንያት አትመስክር፤በከንፈርህም አትሸንግል።

29. “በእኔ ላይ እንደ ሠራብኝ እሠራለታለሁ፤ስለ አድራጎቱም የጁን እመልስለታለሁ” አትበል።

30. በሰነፍ ሰው ዕርሻ በኩል አለፍሁ፤ማስተዋል የጐደለውን ሰው የወይን ቦታ አልፌ ሄድሁ፤

31. በያለበት እሾህ በቅሎበታል፤መሬቱም ዐረም ለብሶአል፤ቅጥሩም ፈራርሷል።

32. ያየሁትን ነገር አወጣሁ አወረድሁ፤ካስተዋልሁትም ትምህርት አገኘሁ፤

33. “ጥቂት ላንቀላፋ፣ ጥቂት ላሸልብ፣እጄን አጣጥፌ ጥቂት ልረፍ” ብትል፣

34. ድኽነት እንደ ወንበዴ፣እጦትም እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 24