ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 24:15-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. በጻድቅ ሰው ቤት ላይ እንደ ወንበዴ አታድፍጥ፤መኖሪያውንም በድንገት አታጥቃ፤

16. ጻድቅ ሰባት ጊዜ እንኳ ቢወድቅ ይነሣልና፤ክፉዎች ግን በጥፋት ይወድቃሉ።

17. ጠላትህ ሲወድቅ ደስ አይበልህ፤ሲሰናከልም ልብህ ሐሤት አያድርግ፤

18. አለዚያ እግዚአብሔር ይህን አይቶ ደስ አይለውም፤ቍጣውንም ከእርሱ ይመልሳል።

19. በጨካኞች ድርጊት አትጨነቅ፤በክፉዎችም አትቅና፤

20. ግፈኛ ተስፋ የለውምና፤የክፉዎችም መብራት ድርግም ብላ ትጠፋለች።

21. ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፤ከዐመፀኞችም ጋር አትተባበር፤

22. ሁለቱም የሚያመጡት መዓት፤ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል?

23. እነዚህም ደግሞ የጠቢባን ምሳሌዎች ናቸው፦በዳኝነት አድልዎ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤

24. በደለኛውን፣ “አንተ ንጹሕ ነህ” የሚለውን፣ሕዝቦች ይረግሙታል፤ መንግሥታትም ያወግዙታል።

25. በደለኛውን፣ “አንተ ጥፋተኛ ነህ” የሚሉት ግን መልካም ነገር ይገጥማቸዋል፤የተትረፈረፈ በረከትም ይወርድላቸዋል።

26. እውነተኛ መልስ መስጠት፣ከንፈርን እንደ መሳም ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 24