ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 23:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የስስታምን ምግብ አትብላ፤ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤

7. ሁል ጊዜ ስለ ዋጋ የሚያሰላ ሰው ነውና፤“ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።

8. የበላሃት ትንሿ እንኳ ታስመልስሃለች፤የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ።

9. ከጅል ጋር አትነጋገር፤የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና።

10. የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ፤አባት የሌላቸውንም ልጆች መሬት አትግፋ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 23