ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 23:28-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. እንደ ወንበዴ ታደባለች፤በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች።

29. ዋይታ የማን ነው? ሐዘንስ የማን ነው?ጠብ የማን ነው? ብሶትስ የማን ነው?በከንቱ መቊሰል የማን ነው? የዐይን ቅላትስ የማን ነው?

30. የወይን ጠጅ በመጠጣት ጊዜያቸውን ለሚያባክኑ ነው፤እየዞሩ ድብልቅ የወይን ጠጅ ለሚቀማምሱ ሰዎች ነው።

31. መልኩ ቀይ ሆኖ፣በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣ሰተት ብሎ በሚወርድበትም ጊዜ፣ ወደ ወይን ጠጅ ትክ ብለህ አትመልከት።

32. በመጨረሻው እንደ እባብ ይነድፋል፤እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።

33. ዐይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤አእምሮህም ይቀባዥራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 23