ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 23:26-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ልጄ ሆይ፤ ልብህን ስጠኝ፤ዐይኖችህም ከመንገዴ አይውጡ፤

27. ዘልዛላ ሚስት ጠባብ ጒድጓድ፣አመንዝራም ሴት ዐዘቅት ናትና፤

28. እንደ ወንበዴ ታደባለች፤በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች።

29. ዋይታ የማን ነው? ሐዘንስ የማን ነው?ጠብ የማን ነው? ብሶትስ የማን ነው?በከንቱ መቊሰል የማን ነው? የዐይን ቅላትስ የማን ነው?

30. የወይን ጠጅ በመጠጣት ጊዜያቸውን ለሚያባክኑ ነው፤እየዞሩ ድብልቅ የወይን ጠጅ ለሚቀማምሱ ሰዎች ነው።

31. መልኩ ቀይ ሆኖ፣በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣ሰተት ብሎ በሚወርድበትም ጊዜ፣ ወደ ወይን ጠጅ ትክ ብለህ አትመልከት።

32. በመጨረሻው እንደ እባብ ይነድፋል፤እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።

33. ዐይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤አእምሮህም ይቀባዥራል።

34. በባሕር ላይ የተኛህ፣በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ የተጋደምህ ትመስላለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 23