ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 23:18-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ለነገ ርግጠኛ አለኝታ ይኖርሃል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።

19. ልጄ ሆይ አድምጥ፤ ጠቢብም ሁን፤ልብህም ከትክክለኛው መንገድ አይውጣ።

20. ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ፣ሥጋ ከሚሰለቅጡ ጋር አትወዳጅ፤

21. ሰካራሞችና ሆዳሞች ድኾች ይሆናሉና፤እንቅልፋምነትም ቡትቶ ያለብሳቸዋል።

22. የወለደህን አባትህን አድምጥ፤እናትህንም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።

23. እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ገንዘብህ አድርግ።

24. የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ጠቢብ ልጅ ያለውም በእርሱ ሐሤት ያደርጋል።

25. አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።

26. ልጄ ሆይ፤ ልብህን ስጠኝ፤ዐይኖችህም ከመንገዴ አይውጡ፤

27. ዘልዛላ ሚስት ጠባብ ጒድጓድ፣አመንዝራም ሴት ዐዘቅት ናትና፤

28. እንደ ወንበዴ ታደባለች፤በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 23