ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 23:12-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ልብህን ለምክር፣ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል ስጥ።

13. ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፤በአርጩሜ ብትገርፈው አይሞትም።

14. በአርጩሜ ቅጣው፤ነፍሱንም ከሞት አድናት።

15. ልጄ ሆይ፤ ልብህ ጠቢብ ቢሆን፣የእኔም ልብ ሐሤት ያደርጋል፤

16. ከንፈሮችህ ትክክሉን ቢናገሩ፣ውስጣዊ ሁለንተናዬ ሐሤት ያደርጋል።

17. ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ነገር ግን ዘወትር እግዚአብሔርን ለመፍራት ትጋ።

18. ለነገ ርግጠኛ አለኝታ ይኖርሃል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።

19. ልጄ ሆይ አድምጥ፤ ጠቢብም ሁን፤ልብህም ከትክክለኛው መንገድ አይውጣ።

20. ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ፣ሥጋ ከሚሰለቅጡ ጋር አትወዳጅ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 23