ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 22:21-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ለላከህ ተገቢውን መልስ ትሰጥ ዘንድ፣እውነተኛውና የታመኑ ቃሎችን እንዳስተምርህ አይደለምን?

22. ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤

23. እግዚአብሔር ይፋረድላቸዋልና፤የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል።

24. ከግልፍተኛ ጋር ወዳጅ አትሁን፤በቀላሉ ቱግ ከሚልም ሰው ጋር አትወዳጅ፤

25. አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ራስህም ትጠመድበታለህ።

26. በዋስትና ቃል እጅ አትምታ፤ለብድር ተያዥ አትሁን፤

27. የምትከፍለው ካጣህ፣የምትተኛበት ዐልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል።

28. የቀድሞ አባቶችህ ያስቀመጡትን፣የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 22