ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 22:12-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።

13. ሰነፍ፣ “አንበሳ ውጪ አለ፤መንገድ ላይ እገደላለሁ” ይላል።

14. የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጒድጓድ ነው፤ እግዚአብሔር የተቈጣውም ይገባበታል።

15. ሞኝነት በሕፃን ልብ ታስሮአል፤የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያርቅለታል።

16. ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።

17. የጠቢባንን ቃል ልብ ብለህ ስማ፤ልብህም ወደ ትምህርቴ ያዘንብል፤

18. በልብህ ስትጠብቃቸው፣ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና።

19. ስለዚህ እምነትህ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን፣ዛሬ አንተን ራስህን አስተምርሃለሁ።

20. የምክርና የዕውቀት ቃል የሆኑ፣መልካም ትምህርቶችን አልጻፍሁልህምን?

21. ለላከህ ተገቢውን መልስ ትሰጥ ዘንድ፣እውነተኛውና የታመኑ ቃሎችን እንዳስተምርህ አይደለምን?

22. ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 22