ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 22:10-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ፌዘኛን አስወጣው፤ ጠብ ይወገዳል፤ጥልና ስድብም ያከትማል።

11. የልብ ንጽሕናን ለሚወድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።

12. የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።

13. ሰነፍ፣ “አንበሳ ውጪ አለ፤መንገድ ላይ እገደላለሁ” ይላል።

14. የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጒድጓድ ነው፤ እግዚአብሔር የተቈጣውም ይገባበታል።

15. ሞኝነት በሕፃን ልብ ታስሮአል፤የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያርቅለታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 22